MassawaTube.com
Welcome
Login / Register

የኣማርኛ ገጽ


 • ታሪክ ደብረ ቢዘን ገዳም

  ደብረ ቢዘን ገዳም . ኣባታችን ጻድቅ ኣቡነ ፊልጳስ ኣባታቸው ኣቡኦም ይርደኣነ እግዚእ ሲባሉ እናታቸው ደሞ ቅድስት መግደላዊት ይባላሉ። የተወለዱበት ጥቅምቲ 9 1319 ዓመተ ምህረት ሲሆን ሕዳር 18 በሓዋርያ ፊልጶስ መታሰቢያ ቀን ስለተጠምቁ ደሞ የክርስትና ስማቸው ፊልጶስ ተባለ ። ጻድቅ ኣቡነ ፊልጶስ የተወለዱበት ቦታ ትግራይ ክፍለ ሃገር ኣውራጃ ኣክሱም ሆኖ እዚ ክፍለ ሃገር ኣውራጃ እንድርታ የሚገኝ ደብረ ጸራቢ ተብሎ በሚጠራ ገዳም ብእጅ ኣቡነ በኪሞስ በ12 ዓመታቸው ምንኩስናን ተቀበሉ። ከምንኩስና በሆላ ወደ ኤርትራ መጥተው ኣውራጃ ሓማሴን ( በኣሁን ኣጠራር ዞባ ማእከል ) ዞባ ዓንሰባ በሚባለው ቦታዎች እየተንቀሳቀሱ ቃለ ወንጌል ኣስተምረዋል ። ከተወሰኑ ዓመታት በሆላ እንደ እግዚኣብሄር ፍቃድ ከዓንሰባ 16 መነኮሳት ኣስከትለው መንገዳቸውን ቀጠሉና ከኣስመራ ጥቂት ኪሎሜትራ ወደሚገኘው ወደ ምጽዋ መንገድ ወደሚወስደው ነፋሲት ወደሚባለው ሃገር ኣከባቢ ከባህር ጠለል 825 ሜትር ወደሚሆነው ረጅም ተራራ ላይ ወጡ፡፡ ከ 1360 -- 1365 ዓመተ ምህረት ሴት የማትገባበት የወንዶች ገዳም መስረተው ስሙንም ደብረ ቢዘን በማለት ሰየመው የኣንድነት ማህበር በማቋቋም ገዳማዊ ህይወታቸውን ከሌሎች መነኮሳት ጋር ጀመሩ ። ከዚ በሆላ ለቤተክርስትያን ተተኪ የሚሆን ሊቃውንት ኣያፈሩ በጾምና በስግደት እግዚኣብሄርን በመማጸን ተጉ፡፡ከዚ በሆላ ጌታችንና ኣምላካችን መድሓኒታችብ እየሱስ ክርስቶስ ተገልጦላቸው እንደዚ ኣላቸው፡-
  ኦ ልጄ ፊሊጶስ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ ሚስጥርና 81 ቅዱሳን መጽሓፍት ገልጬልሃለው ኣላቸው።በመቀጠልም ትምህርትህን ከመምህር ስላልተማርክ ደሞ ፋድል ፊልጶስ ይሁን ስምህ ኣላቸው ። ፋድልጽ ማለት ፊደል ያልቆጠረ ወይ ያልተማረ ማለት ነው። ኣባታችን ኣቡነ ፊሊጶስ ብብዙ ጾምና ጸሎትና ተጋድሎ ከቆዩና ብዙ መነኮሳትና ቅዱሳን ካፈሩ በሆላ ኣምላክ ሊሳርፋቸው ፈለገ። ስምህን የጠራ ዝኽርህን የዘከረ፡ ገዳምህን የተሳለመ፡ በዓመታዊ ዝክርህ ላይ ማህሌት የቆመ፡ጥዋፍ፡ ሻማና ፥ዕጣን የሰጠ ምሬልሃለው በማለት ቃል ኪዳን ገባላቸው። ነሓሴ 5 በ 84 ዓመት ዕድሜቸው
  በ 1403 ዓመተ ምህረት ብሰላም ዓረፉ። ጸሎታቸውና በረከታቸው ኣይለየን!!
  ኣሜን ኣሜን ኣሜን። ******* ምንጭ ገደለ ኣቡነ ፊሊጶስ

  Read more »
 • ድንበር የሰበረ ኣስገራሚ ፍቅር/እውነተኛ ታሪክ

  ባለፈው ሳምንት የጎረቤታቸው የኤርትራውያን ፍቅርን መቆቆም ያልቻሉ በግምት 28 የሚሆኑ የሑመራ ወጣቶች ከጠዋቱ በግምት 2 00 የኣዞ፡መንጋ ሳይበግራቸው የተከዜን ወንዝ ብዋና ኣቆርጠው ኤርትራ ወደሚገኘው ኦምሓጀር ገቡ ።

  ህጋዊ ባልሆነ መንገድና በህብረት መግባታቸው የተጠራጠሩ ነዋሪ ኦምሓጀር ለፖሊስ ኦምሓጀር ኣሰረከቦቸው፡፡የፖሊስ ኣዛዡ ህግ በማይፈቅደው መንገድ ድንበር ለምን እንደጣሱ ሲጠየቁ፡ ኣዝዡንና ህዝቡን ብፍቅር እንባ የምያራጭ ድንቅ ነገር ተናገሩ።

  መልሳቸው እንደዚ ነበር፡-በጣም ስለናፍቅናቹ ሰላም ልንላችሁና ፍቅራችንን ልንገልጽላችሁ ነው ድንበር ጥሰን በኣደገኛ ሁኔታየመጣነው ፡፡ በህጋዊ መንገድ እንዳንመጣ የእግር መንገዱ መከፈት ዘገየብን ኣሉ፡፡ይህን ሓቀኛ የፍቅር ጉዞና መልእክት ከልብየታዘቡ ነዋሪ ኦምሓጀር ኣጅበው ሆቴል ኣፍሪካ ተወስደው በሆቴሉ ባለቤት ሽመንዲ ክፍለ የምሳና የሌላ ነገሮች ግብዣ ተድደረገላቸው።

  በመጨረሻም ለህዝብ ኤርትራ በተለይ ለጎረቤታቸው ህዝብ ኦምሓጀር ያላቸውን ጽኑዕ ፍቅር ገልጸውና ህዝብ ኦምሓጀር በተመሳሳይሑመራ መጥቶ እንዲጠይቃቸው በመማጸንን ከቀኑ 8፡00 በወዲ ሳሙኤል በሚባል ሰው ትራክተር ተሳፍረው እስከ ኣጋማሽ የተከዜድልድይ በህዝብና ፖሊስ ታጅበው በሰላም ተመለሱ፡፡
  #Maሳwino

   

  Read more »
RSS